ኑ፤ የእግዚአብሔርን ፍቅር ቅመሱ።
እንኳን ደኅና መጡ።የአማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አማኞች ልትጎበኙን በመፈለግዎ እጅግ ደስ ብሎናል። በእሁድ ጠዋት የአምልኮ ጊዜ አብረውን እንዲያመልኩ እና የጌታን ባርኮት እንዲካፈሉ እናበረታታዎታለን።
ተልዕኳችን: የአማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ታላቁን ተልዕኮ በመፈጸም ላይ የተመሠረተ ነው (ማቴ ፳፰፡፲፰-፳)። እንዲሁም በኢሳ ፷፩፥፩ እንደተገለጸው ለድሆች የምስራችን እሰብክ ዘንድ፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን፥ የተወደደችውን የጌታን ዓመት እናገር ዘንድ ልኮኛል በሚለው ቃል ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህም መሰረት ሰዎችን በፍቅሩ ወንጌል በመድረስ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና አካሉ ወደ ሆነችው ቤተክርስቲያን ማምጣት እና እርሱን እስኪመስሉ ድረስ በቃሉና በኃይሉ በማሳደግ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ነው።
|