ተልዕኳችን
የአማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ታላቁን ተልዕኮ በመፈጸም ላይ የተመሠረተ ነው (ማቴ ፳፰፡፲፰-፳)። እንዲሁም በኢሳ ፷፩፥፩ እንደተገለጸው ለድሆች የምስራችን እሰብክ ዘንድ፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውሮች ማየትን፥ የተወደደችውን የጌታን ዓመት እናገር ዘንድ ልኮኛል በሚለው ቃል ላይ የተመሰረተ ነው። በዚህም መሰረት ሰዎችን በፍቅሩ ወንጌል በመድረስ ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እና አካሉ ወደ ሆነችው ቤተክርስቲያን ማምጣት እና እርሱን እስኪመስሉ ድረስ በቃሉና በኃይሉ በማሳደግ የክርስቶስ ደቀመዛሙርት ማድረግ ነው።
ግብ
አማኑኤል ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በምታገለግላቸው አገልግሎቶች ሁሉ ግብ አድርጋ የያዘችው መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ያተኩራል።
፩) እግዚአብሔርን ማምለክ (ዘፀ ፳፥፫ ፭፤ ማቴ ፳፪፥፴፯)
፪) ወንጌል ላልደረሳቸው ሕዝቦች የምስራቹን ወንጌል ማዳረስ (ሐዋ ፩፥፰፤ ማር ፲፮፥፲፭)
፫) ለክርስቶስ ደቀመዛሙርትን ማፍራት (ማቴ ፳፰፥፲፱ ፳)
፬) አባላትን በጌታ ቃል በማስተማር፣ በማሳደግ፣ በመምከር በልዩ ልዩ አገልግሎት በማሰማራት፣ ሙሉውን ሰው ለክርስቶስ ማቅረብ (ማቴ ፳፪፥፴፱፤ ቆላ ፩፥፳፰)
፭) የአባላትን ፍቅር እና አንድነት ማጠናከር (ማቴ ፳፪፥፴፱፤ ዩሐ ፲፫፥፴፬ ፴፭)